ተፈልጌ ነው የተወለድኩት ! የስለት ልጅ ስለሆነ ነው ። እንዲህ ያለው በልደቱ ቀን ነበር ይሄን ፅሁፍ ያጋራው ዛሬም ልደቱ ነው ። ይቺን ቀን ምን አልባት ድኜ ከጓደኞቼ ከቤተሶቼ ጋር ተቀላቅዬ በዙሪያ የነበሩትን ሰዎች በልደቴ ቀን አመስግኜ እውላለሁ ብሎ እቅድም ይኖረው ይሆናል እንደዛም የሚያስብ ልጅ ነው ። ለህክምና በሄደበት ሁሉ ተፈልጎ መወለዱን በስለት ወደዚች ምድር መምጣቱ ተስፋ የሚሰጣቸው ቤተሰቦቹ እሱ ህክምና ላይ እያለ ድጋሚ አብሯቸው እንዲያሳልፍ አብሯቸው እንዲሆን ተስለው ይሆናል ..ተፈልጎ ወደዚች ምድር ቢመጣም ሳይፈለግ ግን ከዚች ምድር ለቀቀ ..ወጣትነት ተስፋው ሁሉ አብሮት ሄደ