ዛሬ ደርሶ ሰው መሆንህን ቢያስታውስኝፈገግታህ

Written By :

Posted On :

Share This :

ዛሬ ደርሶ ሰው መሆንህን ቢያስታውስኝ ፈገግታህ ሳይቀር በስባሽ ድምፅህ ሳይተርፍ ተደምሳሽ መሆንህን ቢያስታውሰኝ ሳትጠፋ እንድረሳህ ሸሸሁ ጥለኸኝ ሳትሄድ ትቼህ ጠፋሁ በስምህ እንዳልታጀብ ልቤ ትዝታ እንዳያስብ ታክሲም እሸሻለሁ ገና ምን አይተህ እናዛን ዘፈኖች ስሰማ ጆሮዬ እንዳይከጅል ያንተን መረዋ ድምፅ አምጡልኝ እንዳይል እያለህ እንድረሳህ አዎ እሸሻለሁ ከሄድክማ ምን አቅም ኖሮኝ እንቢ እላለሁ